Fana: At a Speed of Life!

የጃፓን አምራች ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከባለሃብቶች ጋር በጥምረት መስራት በሚቻልባቸው የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች ዙሪያ ለጃፓን አምራች ኢንዱስትሪዎች ልዑካን ቡድን አባላት ገለጻ ተደርጓል፡፡

ከጃፓን አምራች ኢንዱስትሪዎች የተወጣጣ የጃፓን ልዑካን ቡድን የኢንቨስትመንት ኮሚሽንን በመጎብኘት ከምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ጋር ተወያይቷል፡፡

ም/ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ÷በተለይም በመንግስት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እየተሰሩ ያሉ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን በሚመለከት ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገለጻ አድርገዋል፡፡

እንዲሁም ከባለሃብቶች ጋር በጥምረት መስራት በሚቻልባቸው የኢንቨስትመንት ዕድሎችና እና አማራጮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላትም በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በፋይናንስ፣ በአምራች ዘርፍ፣በቴሌኮም፣ በአይ ሲ ቲ እና በአውቶሞቲቭ ዘርፎች ለመሰማራት ያላቸውን ፍላጎት ገጸልጸዋል፡፡

በዘርፉ በሕግ እና በፖሊሲ ዙሪያ ያሏቸውን ጥያቄዎች ለምክትል ኮሚሽነሩ ማንሳታቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ከሚሽኑ ቡድኑ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች ድጋፉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በኢትዮጵያ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስተመንት ዕድሎችና አማራጮችን በጥልቀት እንዲቃኙም ጋብዘዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.