Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተመድ ረዳት ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሃፊ ቻንድራሞሊ ራማናታን ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የካፒታል ኢንቨስትመንት ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና አካል በሆነው የአፍሪካ አዳራሽ እድሳት ፕሮጀክት ዙሪያ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

ሚኒስትር ዴኤታው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ አዳራሽን እንዲጠበቅ እና እንዲታደስ ላደረገው አስተዋፅዖ አመስግነዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኮሚሽን አዳራሽ እድሳት ፕሮጀክት ዋነኛ አካል በመሆኗ በ2011 ዓ.ም 3 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ ለግንባታ የሚሆን በፈቃደኝነት መመደቧን አስታውቀዋል።

ረዳት ዋና ፀሃፊው በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ መንግስት ለተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እንደ አስተናጋጅ ሀገር እያደረገ ላለው ድጋፍ ማመስገናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.