Fana: At a Speed of Life!

ኢ/ር ታከለ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባዎች ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ከሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር ዒድ አልፈጥርን አከበሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በነበረው ችግር ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ከሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የዒድ አልፈጥር በዓልን አከበሩ።
 
ኢንጂነር ታከለ ለበዓል ይሆናቸው ዘንድም ከባለሃብቶች ያሰቧሰቧቸውን የተለያዩ ስጦታዎችን ማበርከታቸውን ገልጸዋል።
 
በመጨረሻም ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋ።
 
በድጋፉም የተለያዩ የምግብ አይነቶች እና ሰንጋ በሬዎችን ያስረከቡ ሲሆን በአካባቢው የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን በማሻሻል የመኖሪያ ቤቶችም ይገነባሉ ብለዋል።
 
የተፈናቀሉ ዜጎችም በተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።
 
በመላው ሃገሪቱ 1 ሺህ 441ኛው የኢድ አልፈጥር በአል እየተከበረ ይገኛል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.