Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የአጎበር እደላና የኬሚካል ርጭት ሥራ መከናወኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የወባ በሽታን ለመከላከል በ46 ወረዳዎች የአጎበር እደላና የኬሚካል ርጭት ሥራ መከናወኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ አቶ ገብረመድህን ክንፉ እንደገለጹት÷የወባ መከላከል ሥራው እየተከናወነ ያለው ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ነው።

እስካሁን ድረስ በተከናወኑ ሥራዎች 1 ነጥብ 3 ሚሊየን የወባ መከላከያ አጎበር ለህብረተሰቡ መታደሉን ገልጸዋል።

በከፍተኛ ወጪ የሚገዛን አጎበር ህብረተሰቡ በአግባቡ በመጠቀም ጤናውን እንዲጠብቅ አስፈላጊው ክተትልና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሰራቱንም ተናግረዋል።

ከአጎበር እደላው በተጨማሪ ከ218 ሺህ በሚበልጡ መኖሪያ ቤቶች ላይ የኬሚካል ርጭት ሥራ እንደተከናወነ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለኬሚካል ርጭቱ ከ1 ሺህ 400 ሌትር በላይ ኬሚካል ጥቅም ላይ መዋሉን ነው ያመላከቱት፡፡

በወረዳዎቹ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማዳረቅና ቆሻሻዎችን በአግባቡ የማስወገድ ሥራዎች መከናወናቸውንም ጠቅሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.