Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን የተለየውን የኤካ ኮተቤ ሆስፒታልን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ ጋር በመሆን በሆስፒታሉ ባደረጉት ጉብኝት የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞችን አበረታተዋል።

ለህክምና ባለሙያዎቹ ባስተላለፉት መልእክትም፥ “በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ከእናንተ ጋር ናት፤ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ከጎናችሁ በመሆን እናደርጋለን በርቱ” ብለዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችም እንኳን አደረሳችሁ በማለት የበግ ስጦታ ያበረከቱ ሲሆን፥ “ይህን ጊዜ አልፈን በጋራ በዓላትን እንደምናከብር እምነቴ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባት ወደ ህክምና ማእከሉ ገብታ በሰላም ለተገላገለች ነብሰ ጡር ሴትም ስጦታን አበርክተዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው እንደገለጹት በሆስፒታሉ ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ነብሰ ጡር እናት ከትናንት በስትያ ልጇን በቀዶ ህክምና በሰላም ተገላግላላች።

“በአሁኑ ወቅትም ህጻኑና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ” ብለዋል።

በብስራት መለሰ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.