Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከህንድ ብሔራዊ ፎረንሲክ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከህንድ ብሔራዊ ፎረንሲክ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምክትል ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ተሻለ ተሾመ ሥምምነቱ በትምህርትና ስልጠና፣ በመምህራን አቅም ግንባታ እና በማማከር ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በርካታ የልህቀት ማዕከሎችን በማቋቋም በህንድ ከስምንት በላይ ካምፓሶችን በመክፈት የማስተማር፣ የማሰልጠን፣ የምርምርና የማማከር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ80 በላይ ሀገራት ተማሪዎችን በተለያዩ ፕሮግራሞች በስኮላርሽፕ ተቀብሎ እያስተማረ እንደሚገኝ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባ ያለውን የፎረንሲክ ሳይንስ ኮሌጅን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እና የልህቀት ማዕከል ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት የህንድ ብሔራዊ የፎረንስክ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ቴክኒካዊ ድጋፍ ለማድረግ፣ ለማማከር፣ የመምህራንና የባለሙያ አቅም በመገንባት ረገድ ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል።
ሥምምነቱን የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ እና የህንድ ብሔራዊ ፎረንስክ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ቻንስለር ዶ/ር ጄ.ኤም. ቪያስ ተፈራርመውታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.