Fana: At a Speed of Life!

ካሜሩን የመጀመሪያዋ የወባ ክትባት ተቀባይ አፍሪካዊት ሀገር ሆነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ካሜሩን የወባ በሽታን ለማጥፋት የምታደርገውን ጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን ማክሰኞ ዕለትም (ጂ ኤስ ኬ) ከተሰኘ ከብሪታንያ የፋርማሲዩቲካል ኩባንያ የወባ ክትባት መቀበሏ ተገልጿል።
 
ይህም ካሜሩንን ክትባቱን በመቀበል የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ያደርጋታል ነው የተባለው።
 
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከ600 ሺህ በላይ ሰዎችን ለህልፈት የሚዳርገውን በትንኝ ተላላፊ በሽታ ለመዋጋት ወሳኝ እርምጃ ነው ተብሏል።
 
በዚህም 331 ሺህ 200 ክትባቶችን የያዘው ማጓጓዣ ያውንዴ ንሲማለን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱ ታውቋል።
 
ይህ በጋና፣ በኬንያ እና በማላዊ የተከናወኑ የሙከራ መርሐ ግብሮችን ተከትሎ አህጉሪቱ ወባን ለመዋጋት የሰጠችውን ትልቅ ቦታ የሚያመላክት ነው ተብሏል፡፡
 
በዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች መካከል አንዱ የሆነው የወባ በሽታ በአህጉሪቱ ወደ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጉ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን ለህልፈት እንደሚዳርግ ተገልጿል።
 
የካሜሩን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ማናውዳ ማላቺ እንደገለፁት የመጀመሪያ ክትባቶች በሀገሪቱ ከሚገኙ 203 የጤና ተቋማት ውስጥ ለ42ቱ እንደሚሰራጭ መናገራቸውን ኒያራ ሜትሪክስ ዘግቧል።
 
የወባ በሽታ ዓለም ላይ በየዓመቱ ከ600 ሺህ በላይ ሰዎችን ለህልፈት እንደሚዳርግ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመላክታል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.