Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል እና ሃማስ እስረኞችን ተለዋወጡ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል እና ሃማስ እስረኞችን መለዋወጣቸው ተሰማ።
 
ሁለቱ አካላት በዛሬው እለት ተግባራዊ ማድረግ የጀመሩት የአራት ቀን የተኩስ አቁም አካል በሆነው ሥምምነት መሰረት ማምሻውን እስረኞች ተለዋውጠዋል።
 
በዚህ መሰረት እስራኤል 39 ፍልስጤማውያንን መልቀቋን ቢቢሲ አስነብቧል።
 
ዛሬ የተለቀቁት እስረኞች በጋዛ ከተያዙት 300 ፍልስጤማውያን መካከል ሲሆኑ፥ የተለቀቁት እስረኞች መካከል 24 ሴቶች እና 15 ታዳጊ ወጣቶች መሆናቸውም ታውቋል።
 
በአንጻሩ ሃማስ ደግሞ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ያገታቸውን 24 ሰዎች የለቀቀ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 13 እስራኤላውያን፣ 10 የታይላንድ እና አንድ ፊሊፒንሳዊ ዜጋ እንደሚገኙበት ዘገባው አመላክቷል።
 
እስራኤል እና ሃማስ በኳታር አደራዳሪነት የአራት ቀናት የተኩስ አቁም መድረሳቸው ይታወሳል።
 
በእነዚህ የተኩስ አቁም በተደረሰባቸው ቀናትም ሁለቱ አካላት እስረኞችን ይለዋወጣሉ ተብሏል።
 
ከዚህ ባለፈም በጋዛ የሚደረገውን ሰብአዊ ድጋፍ ማሳደግና ለንጹሃን ማዳረስም የተኩስ አቁሙ አካል መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።
 
በዛሬው እለትም የህክምና ቁሳቁስ፣ ነዳጅ እና ምግብ የጫኑ ወደ 60 የሚጠጉ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከግብጽ ወደ ጋዛ መግባታቸው ታውቋል።
 
የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ከ200 በላይ ሰዎች በሃማስ እጅ ሲገኙ፥ ከ6 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ደግሞ በእስራኤል የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ይገኛሉ ነው የተባለው።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.