Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ የ18ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድርን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ የ18 ኛውን የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያና የገንዘብ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 19 ኛውን የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ አካሂዷል፡፡

መነሻና መድረሻውን ሰማዕታት ሐውልት በማድረግ ነው በሁለቱም ጾታዎች ውድድሩ የተከናወነው፡፡

ውድድሩን  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ በቀዳሚነት በማጠናቅቅ የወርቅ ሜዳሊያና የገንዘብ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ክለብ ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቁ የገንዘብና የሜዳሊያ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አትሌቲክስ ክለብ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የገንዘብና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸልሟል፡፡

በውድድሩ ከዘጠኝ ክለቦች እና ሥድስት ክልሎችና ከተማ መሥተዳደሮች የተውጣጡ 42 ሴቶች እና  42 ወንዶች በአጠቃላይ 84 አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሌተናንት ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ፣ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እንዲሁም የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ተክላይ ፈቃዱን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው ውድድሩ የተካሄደው፡፡

 

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.