Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ ይገኛል -ከንተባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የከተማ አስተዳደሩ ክንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን ከንቲባዋ ከህዝብ ተመራጮች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ መናገራቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ከተማ አስተዳደሩ ሶስት ዘመናዊ የገበያ ማዕከላትን በመገንባት፣ የገበያ ሰንስለቱን በማሳጠር እና አምራችን ከሸማች ጋር በቀጥታ በማገናኘት ገበያ የማረጋጋት ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

በተጨማሪም በከተማዋ ባሉ 172 የእሁድ ገበያ ስፍራዎች ላይ የምግብ ነክ ምርቶችበተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆኑን ጠቁመው ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ለአቅመ ደካማ የከተማዋ ነዋሪዎች ማዕድ የማጋራት፣ የተማሪዎች ምገባ እንዲሁም የዳቦ ምርት አቅርቦት በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በዘላቂነት የአቅርቦት ችግሩን የሚፈታና በቂ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያቀርብ የሚችል የንግድ ድርጅት በ2 ቢሊየን ብር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.