Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 27ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመቐለ ከተማ ተጀመረ

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 15 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 27ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ተጀምሯል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የክልል ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ሀላፊ ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱ ሲሆን የክልሉ መንግስት ለስፖርቱ እድገት ያላሰለሰ ድጋፍ እንደሚያደር ገልፀዋል ።

በጉባኤው የ26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ በአባላቱ ተመርምሮ ፀድቋል ።

በጉባኤው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጥያቄ በአባላቱ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.