Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የድሮን ጥቃት በዩክሬን ላይ መፈጸሟ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በአንድ ጀምበር ከፍተኛ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት እንዳደረሰች ዩክሬን ገለጸች።
 
አብዛኛዎቹ ኢላማዎችም በሀገሪቱ ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን የዩክሬን አየር ኃይል ገልጿል።
የዩክሬን አየር ሃይል እንደገለጸው ከ75 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) ጥቃት ተፈጽሟል።
 
ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ ከሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የአየር ላይ ጥቃቱን በተመለከተ የተሰጠ ምንም ማረጋገጫ አለመኖሩን አር ቲ ዘግቧል፡፡
በአጠቃላይ 75 ከፍተኛ ጥቃት አድራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወደ ዩክሬን ግዛት መላካቸውን የአየር ኃይል አዛዥ ኮሎኔል ጄኔራል ኒኮላይ ኦሌሹክ በቴሌግራም ገፃቸው ላይ ባጋሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
“ጠላት በዩክሬን እጅግ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸውን ሰው አልባ አውሮፕላኖች አዝምቷል” ያሉት ኮሎኔሉ የጥቃቱ ዋና ኢላማም ኪየቭ እንደነበረች ጠቁመዋል።
የዩክሬን ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በመጠነ ሰፊው የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ሳቢያ በኪየቭ ውስጥ 77 የመኖሪያ ሕንፃዎች እና 120 ተቋማት ያለ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀርተዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.