Fana: At a Speed of Life!

የቻይናው ኤ አር ጄ 21 ጄትላይነር አውሮፕላን 10 ሚሊየን መንገደኞችን በማጓጓዝ ክብረወሰን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የተሰራው ኤ አር ጄ 21 ጄትላይነር የመንገደኞች አውሮፕላን በሰባት ዓመት ውስጥ 10 ሚሊየን መንገደኞችን በማጓጓዝ ክብረወሰን አስመዝግቧል፡፡
 
ቻይና በራሷ የሰራችውና በፈረንጆቹ 2016 በሀገር ውስጥ በረራ ወደ ንግድ አገልግሎት የገባው አውሮፕላን 10 ሚሊየነኛ መንገደኞቹን በትናንትናው ዕለት ይዞ መብረሩ ተገልጿል።
 
21ኛውን ክፍለ ዘመን በሚመጥን መልኩ ለሀገር ውስጥ በረራ የተሰራው ይህ አውሮፕላን ከጓንግዡ ወደ ቻይና ደቡባዊ ጓንግዶንግ ግዛት ጂያንግ 81 መንገደኞችን አሳፍሮ በመብረር ባለፉት ሰባት ዓመታት 10 ሚሊየን መንገደኞችን በአስተማማኝ ሁኔታ አጓጉዟል ተብሏል።
 
ከ400 በላይ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መስመሮችን ከ140 በላይ በሚሆኑ ከተሞች የዘረጋው ጄት ላይነሩ በኢንዶኔዥያም የባህር ማዶ አገልግሎት መጀመሩን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.