Fana: At a Speed of Life!

በሻንጋይ ማራቶን አትሌት ስራነሽ ይርጋ ዳኜ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻንጋይ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ስራነሽ ይርጋ ዳኜ አሸነፈች።

አትሌቷ 2:21:28 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቃለች።

አትሌት ስራነሽ ይርጋ ዳኜን በመከተል ኬንያዊቷ አትሌት ሴሊ ቼፕየጎ ካፕቲች 2:21:55 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

በወንዶች ደግሞ ኬኒያዊው አትሌት ፊሊሞን ኪፕቱ ኪፕቹምባ 2:05:35 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በአሸናፊነት ሲያጠናቅቅ፤ ታንዛኒያዊው አትሌት አልፎንስ ሲምቡ 2:05:39 በሆነ ሰዓት በመግባት በአራት ሰከንድ ልዩነት ውድድሩን ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.