Fana: At a Speed of Life!

ሃማስ 4 ወታደራዊ አመራሮች እንደተገደሉበት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃማስ በጦርነቱ አራት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እንደተገደሉበት አስታውቋል፡፡

የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ አልቃሲም ብርጌድ ባወጣው መግለጫ ÷ በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት አራት ከፍተኛ የሃማስ ወታደራዊ አመራሮች በጋዛ ሰርጥ መገደላቸውን አረጋግጧል፡፡

ከተገደሉት ውስጥም የሰሜን ጋዛ ብርጌድ አዛዥ እና የሃማስ ወታደራዊ ም/ቤት አባል አሕመድ አል ጋንዶር እንደሚገኝበት ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

በእስራኤልና ሃማስ መካከል በተደረገው የአራት ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ሃማስ እስካሁን 41 ታጋቾችን መልቀቁ ተገልጿል፡፡

ተጨማሪ በሃማስ የታጋቱ እስራኤላውያን ዜጎች በዛሬው ዕለት እንደሚለቀቁም ተጠቁሟል፡፡

እስራኤል በበኩሏ ሶስተኛ ቀኑን በያዘው የተኩስ አቁም ፋታ 78 ፍልስጤማውያን እስረኞችን መፍታቷ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል ስምምነቱን ተከትሎ 248 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዛ መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት እስካሁን በጋዛ 14 ሺህ 500 በላይ ዜጎች ለህልፈት ሲዳረጉ÷በእስራኤል በኩል ደግሞ የ1 ሺህ 200 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.