Fana: At a Speed of Life!

በ6 ቢሊየን ብር ወጪ የብረታብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በመቀሌ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6 ቢሊየን ብር ወጪ በኢትዮጵያ እና ቻይና ባለሐብቶች ትብብር የብረታብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በመቀሌ ከተማ ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በ10 ወራት ውስጥ የሚገነባው የብረታ ብረት ማምረቻ የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ- ግብር ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ÷ በትብብር የሚገነባው “ሌጀንድ ብረታብረት ኢንዱስትሪ ኃላፈነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር”ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ አሥፈጊው ድጋፍ ይደረግለታል ብለዋል።

ሌሎች በግልና በማኅበር የተደራጁ ባለሐብቶችም የዚህን የልማት ፕሮጀክት በዓርዓያነት ተከትለው በማልማት ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የብረታ ብረት ማምረቻው 75 በመቶ በኢትዮጵያዊው ባለሐብት ኢንጂነር ያሬድ ተሥፋይ የተሸፈነ ሲሆን÷ ቀሪው 25 በመቶ ደግሞ በቻይናዊው ባለሐብት ሊ ዮን መሸፈኑን የፕሮጀክቱ አስተባበሪ አቶ ሳምሶም ገብረመድህን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሌጀንድ ብረታ ብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ 6 ሺህ ለሚሆኑ ወገኖች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።

የመቀሌ ከተማ ከንቲባ ይተባረክ አመሃም በበኩላቸው÷ ቀጣይ ድጋፋቸው እንደማይቋረጥ አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.