Fana: At a Speed of Life!

በቅርቡ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤክስፖ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ ግብዣ ቀረበላት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ በፖርቹጋል በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤክስፖ ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ ግብዣ ቀረበላት፡፡

የቱሪዝም ሚንስትር ዴዔታ ሌንሳ መኮንን በኢትዮጵያ ከፖርቹጋል አምባሳደር ሊውዛ ፍራጎሶ ጋር በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ለቱሪዝም ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ሥራዎች የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ፖርቹጋል ዝግጁ መሆኗን አምባሳደሯ አረጋግጠዋል፡፡

የፖርቹጋል ዜጎችም ስለ ኢትዮጵያ የቱሪዝም መስኅቦች በቂ መረጃ እንዲኖራቸው እና ሀገሪቱን እንዲጎበኙ ለማድረግ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡

በቅርቡ በፖርቹጋል በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤክስፖ ላይ የቱሪዝም ሚንስቴር ተገኝቶ ኢትዮጵያን እንዲያስተዋውቅ አምባሳደሯ ግብዣ አቅርበዋል::

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.