Fana: At a Speed of Life!

ሴኔቱ ለዩክሬን በሚደረገው ዕርዳታ ላይ ድምፅ እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን እና ለእስራኤል ባቀረቡት በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ድጋፍ ጥያቄ ላይ በታኅሳስ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ድምፅ እንደሚሰጥ የአሜሪካ ሴኔት የአብላጫዎቹ መሪ ቹክ ሹመር አስታወቁ፡፡
 
የባይደን አሥተዳደር÷ ለእስራኤል፣ ዩክሬን እና ታይዋን ያቀረበውን ወደ 106 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ተጨማሪ የብሔራዊ ደኅንነት ጥምር ዕርዳታ ረቂቅ ዕቅድ ለማስፀደቅ እስካሁን ግፊት ማድረግ አለመቻሉም ተገልጿል።
 
በአሜሪካ ከድንበር ደኅንነት ፖሊሲ ለውጦች ጋር በተገናኘ ሪፐብሊካኑ ማንኛውንም ተጨማሪ ገንዘብ ወደ ዩክሬን ለመላክ እንደ ቅድመ ሁኔታ መያዛቸው ማዕቀፉን ለማዘግየት ምክንያት እንደሆነ ሹመር ገልጸዋል፡፡
የሕግ አውጭው ምክር ቤት ዩክሬን ከአሜሪካ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ካላገኘች ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ትግል እንደምትሸነፍ ማስጠንቀቁንም ሹመር ለሴናተሮች በጻፉት ደብዳቤ ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥበት ሴናተሮች ለስብሰባ እንዲገኙ ሹመር ማሳሰባቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡
ይሁን እንጂ የዩክሬን እና የእስራኤል የእርዳታ ማዕቀፍ ከዓመቱ በፊት ይፀድቃል ተብሎ እንደማይታሰብ አንድ የምክር ቤቱ አባል ተናግረዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.