Fana: At a Speed of Life!

የሰሜን ኮሪያ የስለላ ሳተላይት የአሜሪካ ተቋማትን ፎቶ ማንሳቷ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ሳምንት ያመጠቀቻት ወታደራዊ የስለላ ሳተላይት ዋይት ሀውስን ሳይቀር ፎቶ ማንሳቷን ፒዮንግያንግ ገልፃለች፡፡
 
ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካን እና የደቡብ ኮሪያን ኃይል ለመከታተል እንደምትጠቅም የተናገረችላት አዲሷ ሳተላይት የዋይት ሀውስ እና የተለያዩ ሚስጠራዊ የሆኑ የአሜሪካ ወታደራዊ ጣቢያዎችን ፎቶዎች እንዳገኘች ተናግራለች።
 
የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ዋይት ሀውስን ጨምሮ ዋና ኢላማ በሆኑ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ እና የመንግስት ተቋማትን የሳተላይት ምስሎች መመልከታቸውን ፒዮንግያንግ አስታውለች።
 
ኪም ጆንግ-ኡን ይፋዊ የስለላ ሳተላይት የተግባር ዝግጅት ፕሮጀክት በተሳካ ሁኔታ በመካሄዱ ታላቅ እርካታ እንደተሰማቸው ተገልጿል።
 
በተጨማሪም ሳተላይቷ በፓስፊክ ውቅያኖስ ደሴት ላይ የሚገኘውን የዩኤስ አንደርሰን አየር ኃይል ሰፈርን ፎቶ ማንሳቷም ተገልጿል፡፡
 
ሁለት የባህር ኃይል ማዕከሎችን እና በቨርጂኒያ የሚገኘውን የአየር ማረፊያ እንዲሁም የጣሊያን ዋና ከተማ ሮም አካባቢዎችን ፎቶግራፍ እንዳነሳችም አርቲ ዘግቧል።
 
የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ጉዳዩን ማረጋገጥ እንዳልቻሉ እና ፒዮንግያንግም ጥያቄ የሆኑትን ፎቶዎች ይፋ እንዳላደረገች ተናግረዋል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.