Fana: At a Speed of Life!

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንብ እና የመመሪያዎች አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል ለፖሊስ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንብ እና መመሪያዎች አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል ለፖሊስ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ክፍተቶችን በማሻሻል የጋራ ግንዛቤ እና ወጥነት ያለው የህግ አተገባበር ስራ እንዲኖር ለፌደራል፣ለክልል እና ለከተማ ፖሊስ አመራሮች ስልጠናው እየተሰጠ ነው ብለዋል።

ይህ ስልጠና በአተገባበር ላይ የሚታዩ ተግዳሮት እና ክፍተቶች ላይ ውይይት በማድረግ ህጉን መጠበቅ እና መተግበር ላይ ተገቢ ርብርብ እንዲደረግ ያስችለናል ነው ያሉት።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.