Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ጎብኚዎችን በሚስብ ሁኔታ ቅርሶችን በመጠገን ለአገልግሎት እንዲበቁ ይደረጋል ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን ቅርሶች ለጎብኚ በይበልጥ ሳቢ እንዲሆኑ ጥገና በማድረግ ለአገልግሎት እንዲበቁ ይደረጋል ሲል የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ፡፡

“ቱሪዝም ለአረንጓዴ ልማት፣ አረንጓዴ ልማት ለቱሪዝም” በሚል መሪ ሐሳብ የቱሪዝም ቀን በክልል ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ በደሴ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

የቢሮው ኃላፊ ጣሂር መሐመድ በአከባበሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷ የጎብኚ መዳረሻዎችን በማልማት ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ ለማሣደግ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ በርካታ ታሪካዊ፣ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ቅርሶች መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡

በአካባቢው በተፈጥሮም ይሁን በሰው ሠራሽ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን ቅርሶች ጥገና በማድረግ ለአገልግሎት እንዲበቁ ይደረጋልም ነው ያሉት፡፡

ታሪካዊ የመስህብ ሥፍራዎች በአከባበሩ ተሳታፊዎች እንደሚጎበኙም ተመላክቷል፡፡

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.