Fana: At a Speed of Life!

የስትሮክ መንስዔና ምልክቶች

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስትሮክ ወደ አንጎል አካባቢ ያለው የደም ፍሰት ሲዘጋ ወይም በአንጎል ውስጥ ያለው የደም ቧንቧ ሲበጠስ የሚከሰት ህመም ነው።

ታዲያ የስትሮክ ህመም ምልክቶች ምንድናቸው?

የስትሮክ ምልክቶች የፊት መውደቅ፣ የክንድ ድክመት፣ የንግግር ችግር፣ የአንድ ወይም የሁለቱም አይኖች የማየት ችግር እና ሚዛንን አለመጠበቅ ወይም መንገዳገድ እና ከባድ ራስ ምታት የሚጠቀሱ ሲሆን እነዚህ ምልክቶች ካጋጠሙ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።

በተለይ ደግሞ አንዳንድ ሴቶች ላይ እንደ ድካም፣ ማቅለሽለሽ፣ የሰውነት መዛል፣ ማስታወክ ወይም የማስታወስ ችግር ያሉ ስውር የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ሊስተዋሉባቸው ይችላል።

ማጨስ፣ የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል መጠን መጨመር ደግሞ ስትሮክን ሊያስከትሉ የሚችሉ መንስዔዎች ናቸው፡፡

ነገር ግን ለሴቶች ልዩ የሆኑ ሌሎች መንስኤዎች ያሉ ሲሆን÷ እነዚህም አንዳንድ የሆርሞን ዓይነቶችን መጠቀም፣ ልጅ መውለድ፣ እርግዝና፣ የወሊድ መከላከያ ክኒኖች እና የማይግሬን ራስ ምታት መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.