Fana: At a Speed of Life!

በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የሙያ ማማከርና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መመሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የሙያ ማማከርና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መመሪያ ይፋ አደረገ።

መመሪያው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት(ጂ አይ ዜድ) እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል፡፡

መመሪያው በዘርፉ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያሻሽልና ተማሪዎች ያላቸውን ክህሎት አውጥተው እንዲጠቀሙ አቅም የሚፈጥር መሆኑም ነው የተጠቆመው።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር አማካሪ ተሾመ ለማ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ÷መመሪያው ተማሪዎች ሙያዊ ክህሎታቸውን ተጠቅመው ውጤታማ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል ።

ወጣቶች በዕውቀት፣ በልምድ፣ በራስ አገዝ የሥራ ክህሎት ብቁ እንዲሆኑ፣ የሥራ ፈጠራ ስትራቴጂዎችን እንዲያጤኑና ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያላቸውን ልምድ እንዲያዳብሩም ያስችላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት(ጂ አይ ዜድ) የኢትዮ-ጀርመን የትምህርትና ሥልጠና መርሐ-ግብር አስተባባሪ አሊ ሙሃመድ ካሃን በበኩላቸው ÷መመሪያው በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የሚያልፉ ወጣቶችንና ሥራ ፈጣሪዎችን ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.