Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠር የሚያስችል አሰባሳቢ ትርክት መገንባት ያስፈልጋል- አቶ ኦርዲን በድሪ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠር የሚያስችል አሰባሳቢ ትርክት መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡

አቶ ኦርዲን በድሪ በአርባ ምንጭ የስልጠና ማዕከል እየተሰጠ በሚገኝው የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ላይ ተገኝተው ከመንግስት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት የተዛቡ ትርክቶችን በማስተካከል ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠር የሚያስችል አሰባሳቢና የጋራ ትርክት መገንባት እንደሚስፈልግ ገልጸዋል።

አገራዊ ኢኮኖሚያዊ፣ የሰላምና ደህንነት፣ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ፣ የጊዜና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁም ትኩረት የሚሹ አገራዊ፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ አመራሩ በቂ ግንዛቤ በመያዝ የጋራ አቋም እንዲፈጠር የሚያደርጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ይህም ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ የኢትዮጵያ እዳዎችን በመቅረፍ ወደ ምንዳና ሃብት ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ማንሳታቸውን ከሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.