Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጥላው የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃፓን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጥላው የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  ማንሳቷን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺዞ አቤ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ ሲደረግባቸው የነበሩ አከባቢዎች ከዛሬ ጀምሮ ተነስቷል ሲሉ ነው ይፋ ያደረጉት።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት ጠንካራ መስፈርት አለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ ይሄ መስፈርት በመሟላቱ አዋጁ ተነስቷል ብለዋል።

ከፈረንጆቹ ሚያዝያ ወር ጀምሮ በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተላለፈ በኋላ የቫይረሱን ስርጭት የመቆጣጠር ስራ ሲሰራ ቆይቷልም ነው ያሉት።

ጃፓን ጥላው የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ ማንሳት መጀመሯ የሚታወስ ነው።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ጃፓን 16 ሺህ 50 የኮሮና ቫይረስ ተያዦች እና 820 ሞት በማስመዝገብ ጠንካራ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት አንፃር ዝቅተኛ ቁጥር አስመዝግባለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.