Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ሊመዘበር የነበረ ከ110 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 19 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ሊመዘበር የነበረ ከ110 ሚሊየን ብር በላይ የክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከተቋቋመው የፀረ ሙስና ኮሚቴ ጋር በመተባበር ማዳን መቻላቸው ተገለጸ፡፡

በ2015 በጀት ዓመት ሊመዘበር የነበረን ከ51ሚሊየን ብር በላይ በክትትል ቀድመው ማዳን መቻላቸውም ነው የተመላከተው፡፡

ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው ገንዘብ ደግሞ ከተመዘበረ በኋላ እንዲመለስ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ዘላለም ለማ ይህን ጋዜጣዊ መግለጫ የሠጡት በክልሉ እየተከበረ በሚገኘው የዓለም የፀረ ሙስና ቀን ላይ ነው፡፡

ኮሚሽነሯ የመንግሥትና የሕዝብ ሐብት ከመመዝበሩ በፊት አስቀድሞ መከላከል ላይ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

አሁን ላይ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ 136 ሰዎች ታስረዋልም ነው ያሉት፡፡

ከአፈር ማዳበሪያ ጋር በተያያዘ ለአርሶ-አደሩ መቅረብ የነበረበትን ማዳበሪያ ባለማድረስና በመመዝበር 127 ሰዎች በሕግ ተጠያቂ መደረጋቸውንም አስረድተዋል።

የተመዘበረ ጥሬ ገንዘብ ከማስመለስ በተጨማሪ በዓይነት የሚገለጹ በርካታ ሐብቶችን ማዳን መቻሉንም አንስተዋል።

በብርሃኑ በጋሻው እና ታመነ አረጋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.