Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ሲያሸንፍ ወላይታ ድቻና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ውድድሮች ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የኢትየጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ወላይታ ድቻ እና ድሬዳዋ ከተማ 9 ሰዓት ላይ ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ለወላይታ ድቻ ቢንያም ፍቅሩ በ24ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር÷ ድሬዳዋ ከተማን አቻ ያደረገችዋን ግብ ደግሞ ተመስገን ደረሰ በ61ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ሀምበሪቾ ዱራሜን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግቦች ናትናኤል ገ/ጊዎርጊስ ፣ ጌታነህ ከበደ እና ምኞትደበበ አስቆጥረዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.