Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት የምታደርገውን ጥረት አጋር አካላት እንዲደግፉ ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት ለምታደርገው ጥረት አጋር አካላት እና መንግሥታት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበች፡፡

በዱባይ እየተካሄደ ከሚገኘው 28ኛው ዓለም አቀፍ የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ጎን ለጎን የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ውይይት ተካሂዷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊን ጨምሮ የስምንት ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በዚሁ መድረክ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ የኢትዮጵያን የባሕር በር አቋም አሳውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የዓየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቀነስ እየሠራች መሆኗን ገልጸው÷ ለአብነትም የኢትዮ -ጂቡቲ የምድር ባቡር በኤሌክትሪክ ኃይል እንዲንቀሳቀስ ማድረግ መቻሏን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የዓየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በተሳካ ሁኔታ እያከናወነች መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

እንዲሁም ከኢነርጂ ልማት ዘርፍ አኳም በታዳሽ ኃይል ላይ ትኩረት ማድረጓን ነው ያስረዱት፡፡

የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ለትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ከፍተኛ ወጭ አንደሚያወጡ ጠቅሰው÷ በተጨማሪም ለዓየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ከፍተኛ ተጋላጭ መሆናቸውን በመድኩ አቅርበዋል፡፡

በመሆኑም አጋር አካላት እና መንግሥታት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው በውይይ መነሳቱን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት የምታደርገውን ጥረት የልማት አጋሮች እና መንግሥታት እንዲደግፉ ጥሪ ማቅረባቸውንም አመላክተዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.