Fana: At a Speed of Life!

የመድሐኒትና ሕክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ሰንሰለት መረጃ መከታተያ ሰሌዳ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የመድሐኒትና የሕክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ሰንሰለት መረጃን የሚያሳይ “ዳሽ ቦርድ” ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

ይፋ የተደረገው “ዳሽ ቦርድ” ውሳኔ ሰጪ አካላት አጠቃላይ የአቅርቦት ሰንሰለቱን በቀላሉ በመከታተል በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ እንዳሉት፤ ዳሽ ቦርዱ የአቅርቦት ሰንሰለት ስርዓትን ለማጠናከር ያግዛል።

በስራ ላይ ያሉት እንደ ዳጉ፣ ሜምስና ቪታስ ያሉ የመረጃ ስርዓቶች ለሀገር አቀፉ ዳሽ ቦርድ የመረጃ ግብዓት መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ዳሽ ቦርዱ ጠንካራ እንዲሆን እየተካሄዱ ያሉ አሰራሮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በጤና ሚኒስቴር የመድሐኒትና ሕክምና መሳሪያዎች መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ረጋሳ ባይሳ በበኩላቸው÷ ዳሽ ቦርዱ ያጋጥም የነበረውን የተቀናጀ የመረጃ እጥረት፣ ደካማ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት እንዲሁም የመረጃ አጠቃቀም ችግርን በመፍታት የተሻለ አሰራር እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡

ዳሽ ቦርዱ በሁለት ዙር ወደ ስራ እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን÷በመጀመሪያው ዙር በአቅርቦት ሰንሰለት እና በመድሐኒት ቁጥጥር ዘርፍ እንደሚጀመር መገለጹን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.