Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በስልጠና ላይ የሚገኙ የሥራ ሃላፊዎች የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡና በአዲስ አበባ ማዕከል በስልጠና ላይ የሚገኙ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎችንና ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ለሚ እንጀራ ፋብሪካ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከላት፣ የአድዋ ዜሮ ዜሮ ሙዚየም ፕሮጀክትና የመንገድ ፕሮጀክቶች በሰልጣኞቹ ተጎብኝተዋል።

እንዲሁም የመንገድ አካፋይና የመንገድ ዳርቻ የአረንጓዴ ልማቶችን እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩ በዘጠና ቀናት ገንብቶ ለነዋሪዎች ያስረከባቸውን የመኖሪያ ቤቶች እንደጎበኙ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የተጎበኙት የልማት ስራዎች በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻሉና ቀጣዩን የብልጽግና ጉዞ ያሳዩ መሆናቸውን እንደተመለከቱ ሰልጣኞቹ እንደተናገሩ ተጠቅሷል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.