Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሚተከሉ ማስታወቂያዎች ዲጂታል እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በዋና ዋና መንገዶችና አደባባዮች ላይ የሚተከሉ የውጭ ማስታወቂያዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ዲጂታል እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ፡፡

ከተማዋን ከሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ጋር ተወዳዳሪና ተመራጭ ለማድረግ የውጭ ማስታወቂያዎችና የሕንጻ አጥሮች ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ  እንዲሆኑ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የከተማዋ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ÷ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በዋና ዋና መንገዶችና አደባባዮች ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ደረጃቸውን የጠበቁና እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በተለይም ጥራታቸውን ያልጠበቁ ማስታወቂያዎች ከዋና ዋና መንገዶችና አደባባዮች እንዲነሱ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

ተቋሙ በዚህ አመት የሕንጻ አጥሮችንና ፓርኪንጎች ጥራትና ደረጃ ለማስጠበቅ እየሰራ እንደሚገኝ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.