Fana: At a Speed of Life!

በጥናት የተመሰረቱ የግጭት መፍቻ መንገዶችን በመተግበር ዘላቂ ሰላም የመገንባት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – የሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥናት ላይ የተመሰረቱ የግጭት መፍቻ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ ዘላቂ ሰላም የመገንባት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሰላም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ የግጭት መንስኤዎችን በመለየት የመፍትሄ አማራጮችን ያመላከተ ጥናት ይፋ አድርጓል።

በመድረኩ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶ/ር)÷ ጥናቱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጥናቱ የተከሰቱ ግጭቶች መነሻና አባባሽ ምክንያቶችን እንዲሁም መፍትሄዎቹን በዝርዝር ያመላከተ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

የግጭቶች ዋነኛ መነሻ ምክንያት የተለያዩ ቢሆኑም በጥናቱ መሰረት መዋቅራዊ የሆኑና በአግባቡ መፈታት ያለባቸው ችግሮች እንዳሉ ተመላክቷል ብለዋል።

የውይይት ባህል ይበልጥ መዳበር እንዳለበትና የፖለቲካ ባህሉም ውይይትን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

በጥናት ላይ የተመሰረቱ የግጭት መፍቻ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ ዘላቂ ሰላም የመገንባት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በጥናት ከሚለዩት የግጭት መፍቻ መንገዶች በተጨማሪ ባህላዊ የግጭት መፍቻ አማራጮችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር በመንግስት የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉ ሆነው የሰላም ባለቤቱ ህዝቡ በመሆኑ በዚህ ዙሪያም ብዙ መስራት እንደሚጠይቅ በመድረኩ ተነስቷል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.