Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በዛሬው እለት ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

9 ሰዓት ላይ በተካሄደ የመጀመሪያው ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የአዳማ ከተማ ግቦችን ሀቢብ መሐመድ እና ቢንያም አይተን ሲያስቆጥሩ÷አንተነህ ተፈራ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

እንዲሁም 12 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማሸነፊያ ሁለት ጎሎችን ሱሌማን ሐሚድ እንዲሁም ፈቱዲን ጀማል ደግሞ አንድ ጎል አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.