Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ስራ ድርጅት አባልነት 100ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል እና የብሔራዊ የአሰሪና ሰራተኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ )”ማህበራዊ ምክክርና ምርታማነት ለማህበራዊ ፍትህ “በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ የ100ኛ ዓመት የዓለም ስራ ድርጅት አባልነት መታሰቢያ በዓል እና የብሔራዊ የአሰሪና ሰራተኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ አመታት ከዓለም የስራ ድርጅት ጋር በመሆን ምቹ የስራና ጤናማ ሁኔታ ለመፍጠር ስራዎችን ስትሰራ ቆይታለች ።

ያለፉት 100 አመታት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ቢሆንም ተግዳሮቶች እንደነበሩም ነው የገለጹት።

የአሰሪዎችን እና ሰራተኞች ግንኙነትን የተሻለ ለማድረግ እና አንዱ ያለ አንዱ ምንም እንዳይደለ የግንዛቤ ስራዎችን በመስራት ምቹ የስራ ሁኔታን ለመፍጠር መሞከሩንም አንስተዋል።

የአሰሪና ሰራተኛ ጉባዔው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ስኬቶች የሚገመገሙበት፣ ልምዶች የሚቀመሩበት እና ለዘርፉ መጠናከር የሚያግዙ ምክረ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት ነው ተብሏል።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከዓለም የሥራ ድርጅት ጋር ባለው ትብብር የተገኙ ስኬቶች በሚጠናከሩበት እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በሚፈቱበት አቅጣጫ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.