Fana: At a Speed of Life!

የጂቡቲ ፕሬዚዳንት በሀገሪቱ በተዘጋጀው ዓለም ዓቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ የኢትዮጵያን የወጪ ምርቶች ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ እና ቀዳማዊት እመቤት ካድራ መሐሙድ በሀገሪቱ በተዘጋጀው ዓለም ዓቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ኢትዮጵያ ይዛ የቀረበችውን የወጪ ንግድ ምርቶች ጎብኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ እና ቀዳማዊት እመቤት ካድራ መሐሙድ የኢትዮጵያን ቡና ጨምሮ የወጪ ምርቶችን የጎበኙት በጂቡቲ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው ዓለም አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት ነው፡፡

በፈረንጆቹ ከታህሳስ 3 እስከ 10 ቀን 2023 ድረስ በሚቆየው 3ኛው የዓለም አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ የኢትዮጵያን የወጪ ምርቶች እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለዓለምአቀፉ የንግድ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.