Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው ከ889 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል እያሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከ889 ሚሊየን 539 ሺ ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል እያሠራጨ መሆኑን  ገለጸ።

የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ስርጭትና ተሽከርካሪ ስምሪት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሺፈራው በቀለ ÷  መጪው የክረምት ወቅት እንደመሆኑ መጠን ከወዲሁ በወባ ምክንያት የሚከሰተውን ህመምና ሞት ለመከላከል ከፍተኛ የወባ ስርጭት ባለባቸው አከባቢዎች በአማራ፣ ትግራይ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ፣ አፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች ላይ 928 ሺህ 011 ኪሎ ግራም የጸረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ዛሬ መሰራጨት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ከዚያም ባለፈ ከ 5 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ለወባ በሽታ መከላከያ የሚውል የመኝታ አልጋ አጎበር እየተሰራጨ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ ዜናም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ቫይረሱ ሊያመጣቸው የሚችላቸውን አስከፊ የጤና ቀውሶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአጠቃላይ በዚህ ሁለት ወራት ውስጥ ኤጀንሲው ከ5 ነጥብ 8 ቢሊዬን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች መሰራጨታቸውን ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.