Fana: At a Speed of Life!

ሕዝቡ የሕዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ በአንድነት እንዲቆም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ በአንድነት እንዲቆም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠየቀ።

የጉባዔው የበላይ ጠባቂዎችና አባላት የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር፣ በቀለም፣ በኃይማኖት፣ በብሔርና በፖለቲካ አቋም ሳይለያይ ግንባታውን ለማጠናቀቅ በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

መንግሥትም ከተፋሱስ ሀገራት ጋር የሚያደርገውን ድርድር በሰላማዊ መንገድ በመቀጠል ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበሩን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም የጉባዔው የበላይ ጠባቂዎች አሳስበዋል።

የሃይማኖት አባቶቹ ግድቡ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የልማትና የዕድገት ተስፋ መሆኑን አስታውሰው መንግሥት የሚያደርገውን ድርድር አጠናክሮ መቀጠል አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.