Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን መከበር ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመገንባት ሚናው የጎላ ነው – አቶ ሙስጠፌ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበር የምናስባትን አካታችና ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመገንባት ሚናው የጎላ ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ።

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የ18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባባርን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በጅግጅጋ መከበር ልዩ ትርጉም እንዳለው አንስተዋል።

በዓሉ በታቀደው መልኩ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑን አብራርተው፤ የጸጥታ እና ሌሎች አገልግሎቶች ሰጪ ተቋማትም አስተማማኝ ዝግጅት አድርገው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመዋል።

በዓሉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህላቸውን እንዲለዋወጡ እና ማንነታቸውን እንዲያሳዩ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል።

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል መከበር አካታችና ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመገንባት ሚናው የጎላ ነው ሲሉም አውስተዋል።

በዓሉን ለማክበር ጅግጅጋ ለገቡ እንግዶች የ’እንኳን ደህና መጣችሁ’ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ሙስጠፌ፤ በዓሉ በክልሉ መከበሩ ለቀጣይ በርካታ ልምዶችና ተሞክሮዎችን እንደሚያስገኝ ተናግረዋል።

የበዓሉ ታዳሚዎች ደህንነታቸው ተጠበቆ በዓሉን እንዲያከብሩ እና ቆይታቸው ያማረ እንዲሆን በሁሉም ዘርፍ አስተማማኝ ዝግጅት መደረጉን አረጋግጠዋል።

ከለውጡ ወዲህ በክልሉ ዘላቂ ሰላም መሥፈኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በበርካታ ዘርፎች ስኬቶች መመዝገባቸውን አስረድተዋል።

በተለይም በጤና ተቋማት፣ በመንገድ ልማት፣ በመጠጥ በውሃ ተደራሽነት፣ በከተማ ልማትና ሌሎች ዘርፎች በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

በመላኩ ገድፍ
#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.