Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ ጀግኖችና ህጻናት አምባ ለመከላከያ ዋና ጤና መምሪያ የህክምና ቁሳቁሶችን አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ጀግኖችና ህጻናት አምባ ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች ያገኛቸውን የህክምና ቁሳቁሶች ለመከላከያ ዋና ጤና መምሪያ አስረክቧል።

የህክምና ቁሳቁሶቹን የብሔራዊ ጀግኖችና ህጻናት አምባ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ሻለቃ ተስፋዬ ወንድሙ ለመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ጥጋቡ ይልማ አስረክበዋል።

ድጋፉ በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ የመከላከያ ሆስፒታሎች ይሰራጫል ነው የተባለው።

ድጋፍ የተደረጉት የህክምና ቁሳቁሶቹ፣ የንጽህና መጠበቂያዎች፣ ዊልቼርና ሌሎችንም ያካተተ እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.