Fana: At a Speed of Life!

በአፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ በ18ኛው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ላይ ለመታደም ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብቷል።

አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገርና ልኡካን ቡድናቸው ጅግጅጋ ገራድ ዊል ዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እና የክልሉ ክፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች አቀባበል አድገውላቸዋል፡፡

የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል “እኩልነትና ብዙኀነት ለሃገራዊ አንድነት”በሚል መሪ ሃሳብ በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው፡፡

በዛሬው ዕለትም በዓሉን አስመልክቶ ‘የአብሮነት’ ቀን በሚል የተለያዩ ሁነቶች ተካሒደዋል።

18ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር ቆይቶ የፊታችን ሕዳር 29 ቀን የማጠቃለያ መርሐ ግብሩ የሚካሄድ ይሆናል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.