Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ከደረጃ በታች የሆኑ 17 የግል ኮሌጆች መዘጋታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልሉ ከደረጃ በታች የሆኑና በህገ-ወጥነት የተገመገሙ 17 የግል ኮሌጆችን ማዘጋቱን የክልሉ ስራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የመንግስት እና የግል ኮሌጆች የ2015 ዓ.ም ክትትልና ግምገማ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓዋል።

የቢሮዉ ሀላፊ ሀገረፅዮን አበበ በወቅቱ እንደገለፁት÷ ከደረጃ በታችና በህገ-ወጥ መንገድ ሲያሰለጥኑ የቆዩ 17 የግል ኮሌጆች እንዲዘጉ ተደርገዋል።

እንዲሁም 7 ኮሌጆች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማሻሻል ከቻሉ ማሰልጠን ይችላሉ ተብለው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ነዉ ያሉት።

ስለሆነም አትላስ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ፊሪላንድ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ራዲካል ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ስፓርክ አፍሪካ አለታ ጩኮ፣ ዩኒክ ስታር አለታ ጩኮ፣ ዛክቦን ኮሌጅ በንሳ ዳዬ፣ ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ዩኒክ ስታር ኮሌጅ በንሳ ዳዬ፣ ኦሞ ቫሊ ኮሌጅ ሞሮቾ፣ አፍኒ ፎር አፍሪካ አለታ ወንዶ፣ ዩኤስ ኮሌጅ በንሳ ዳዬ፣ ዩኒክ ስታር ኮሌጅ አርቤጎና፣ ፋርማ ኮሌጅ ለኩ፣ ሮሚክ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ካይዘን ዲዲ ኮሌጅ ሁላ ወረዳ፣ ዩኒክ ስታር ኮሌጅ ለኩ፣ ሂሊኬን ኮሌጅ ጭሬ ከነገ ጀምሮ የሚዘጉ ኮሌጆች መሆናቸው ተገልጿል።

ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ኮሌጆች ደግሞ ሰባት ሲሆኑ እነዚህም፦ ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ፉራ ኮሌጅ ይርጋለም፣ ዳዲሞስ ኮሌጅ ለኩ፣ እናት ኮሌጅ አለታ ወንዶ፣ ታቦር ቢዝነስ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ዛይን ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ኒው ግሎባል ቪዥን ኮሌጅ ሀዋሳ ናቸው ተብሏል።

ገበያ ላይ ተፈላጊነት የሌላቸው ናቸው የተባሉ የሙያ ዘርፎች እንደሚዘጉም ሃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡

በደብሪቱ በዛብህ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.