Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በማስመልከት ሀገር አቀፍ ሲምፖዚዬም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ሕዳር፣28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት ሀገር አቀፍ ሲምፖዚዬም በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሲምፖዚዬሙ ሚኒስትሮች፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አመራሮች፣ የክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

”ኮንሶሲዬሽናል ዴሞክራሲ፤ ጽንስ ሐሳባዊ ዳራውና ኢትዮጵያዊ እሳቤው” በሚል የተዘጋጀ ጽሑፍ ለውይይት ቀርቧል።

በመድረኩ ብሔር ተኮር ብዝሃነት ዘለቄታዊ አለመረጋጋትን ወይም ብሔር ወለድ ጭቆናን በማያስከትል ሁኔታ ወደ ዴሞክራሲ ለማሸጋገር የሥልጣን መጋራት ስልትን መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተነስቷል።

በኢትዮጵያ የሀገረ መንግስት ቅርጽ ላይ ውሳኔ መድረስ የሚገባው ሁሉን አቀፍ ውይይት በማድረግ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባ በጽሑፉ ተብራርቷል።

ኮንሶሲዬሽናል ዴሞክራሲ የታቀደለትን አላማ ሊያሳካ የሚችለውም አጥጋቢ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሲኖርና አብሮነት ሲዘረጋ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የመብት መከበርን የሚከታተሉ ገልተኛ ተቋማትን ማጠናከርና ሥራቸውን በነጻነት እንዲሠሩ ማስቻል አስፈላጊ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በመቻቻልና በመከባበር ላይ የተመሠረተ ጠንካራ አንድነትን መፍጠር ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ተመላክቷል።

በመላኩ ገድፍ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.