Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ዋዜማ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ሕዳር፣28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ዋዜማ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ የሁሉም ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ተወካዮች ተገኝተዋል።
በዚህም ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አብሮነታቸውን የሚያንጸባርቁ ሁነቶችን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
በመድረኩ ተሳታፊዎች የእርስ በርስ የባህል፣ እምነት እና ማንነት ልውውጥ እያካሄዱ ነው።
በመርሐ ግብሩ መጨረሻም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ማዕድ የሚቋደሱ ይሆናል።
በነገው ዕለትም በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ የሚገኘው 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች በዓል ማጠቃለያ መርሐ ግብር ይካሄዳል።
በመርኃ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በዓሉ ባማረ መልኩ እንዲዘጋጅ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ተገኝተዋል።
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.