Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል እና ባህር ዳር ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰባተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው እለት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
 
ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ መቻል ከአዳማ ከተማ ተገናኝተዋል።
 
አዳማ ከተማ ጨዋታውን በቢኒያም አይተን ጎል 1 ለ 0 መምራት ቢችልም ተከታትለው በተቆጠሩበት ሁለት ጎሎች 2 ለ 1 ተሸንፏል።
 
ሳሙኤል ሳሊሶ እና ሽመልስ በቀለ ለመቻል የድል ጎሎችን አስቆጥረዋል።
 
ምሽት በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ባህር ዳር ከተማ ከሐዋሳ ከተማ ተገናኝተው ጨዋታው በባህር ዳር ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።
 
ባህር ዳር ከተማ ከዕረፍት በፊት ቸርነት ጉግሳ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ጨዋታውን 2 ለ 1 አሸንፏል።
 
ታፈሰ ሰለሞን ደግሞ በመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ የሐዋሳ ከተማን የማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.