Fana: At a Speed of Life!

ሃማስ በወሰደው እርምጃ ፍልሥጤማውያን ሊቀጡ አይገባም – አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃማስ በእስራዔል በፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት ፍልሥጤማውያን ገፈት ቀማሽ መሆን እንደሌለባቸው የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሳሰቡ፡፡

‘አረመኔያዊ ድርጊትን በአረመኔያዊ ድርጊት መመለስ ኢ-ሰብዓዊ’ እንደሆነና የእስራዔል ድርጊትም ከሰብዓዊ ሕግ ጥሰት አንፃር ወንጀል መሆኑን አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አክለውም ÷ የጋዛ ሕዝብ መሠረታዊ ነገሮችን ማግኘት ሳይሆን በሕይወት የመኖር ኅልውናው እንኳ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ነው ያሉት፡፡

“በጋዛ የትኛውም ቦታ ለደኅንነት አሥጊ ነው” ሲሉም ነው የጉዳዩን አሳሳቢነት ያስረዱት፡፡

አክለውም የጋዛ ሕዝብ ሁሉንም ነገር አጥቶ ሲሚንቶ ላይ እያደረ እና የሚበላ ጠፍቶ በረሃብ እየተቀጣ ነው ብለዋል፤ ይህ ፍጹም ተገቢ አይደለም ሲሉም ኮንነዋል፡፡

ሃማስ በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 ላይ የወሰደውን የመጀመሪያ ነው የተባለውን ጥቃት እንደሚያወግዙ ገልጸው፥ ቡድኑ ያገታቸውን እስራዔላውያን በአስቸኳይ እንዲለቅም ጥሪ አቅርበዋል።

አሁን ላይም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በጋዛ በፍጥነት የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በተባበሩትአረብ ኢሚሬቶች በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምጽ ለመስጠት ሊቀመጥ መሆኑን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.