Fana: At a Speed of Life!

ይህ የበዓል ዋዜማ ምሽት ከዚህ ቀደም የነበረውን የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት እሴት ወደነበረበት እንዲመለስ ቃል የምንገባበት ነው – አቶ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ይህ የበዓል ዋዜማ ምሽት ከዚህ ቀደም በUገራችን የነበረውን የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት እሴት ወደነበረበት እንዲመለስ ቃል የምንገባበት ነው ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ክብረበዓልን ለመታደም በጂግጂጋ ለተሰባሰቡ የክብር እንግዶች እና የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ግቢ የእራት ግብዣ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በየዓመቱ መከበር አሁን ላለው እና ወደፊት ለሚተካው ትውልድ አንድነትና ትስስር መጠናከር የጎላ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

በዓሉ ሕዝቦች ልምዳቸውን፣ ተሞክሯቸውንና ባህላቸውን በመለዋወጥ ዴሞክራሲያዊ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ ያደርጋል ማለታቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል።

ከለውጡ በኋላ የተከበሩ በዓላት ሕዝቦች ለረዥም ዘመናት ይዘውት የቆዩትን አብሮነት እንዲያጸኑ፣ ከልዩነት ይልቅ አንድነት እንዲጎለብት፣ ከመራራቅ ይልቅ መቀራረብ እንዲጠናክር፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር እንዲሰፍን፣ በጥርጣሬ ከመተያየት ይልቅ መተማመን እንዲኖርና በሕገ መንግሥቱና በፌዴራል ሥርዓቱ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲፈጠር የሚያስችሉ ሰፊ ሥራዎች መሠራታቸውንም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.