Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያ እንቅስቃሴን ለማስጀመር የጸደቀውን አዋጅ ወደ ተግባር የመቀየርና ባለስልጣኑን የማደራጀት ስራ እየሰራ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የህግ ማዕቀፍ እና መመሪያ መጨረሳቸውን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፥ 15 አሻሻጮች ፍቃድ የሚያገኙበት አሰራር ተዘርግቷል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ገበያ ላይ ሊገዙ እና ሊሸጡ የሚችሉ ኩባንያዎች ዝርዝር ወጥቶ የማብቃት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አምስት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተለይተዋል ነው ያሉት። በተጨማሪም ሰባት አዳዲስ መመሪያዎች መውጣታቸውንም ገልጸዋል።

በአልማዝ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.