Fana: At a Speed of Life!

በህዳሴ ግድብ ግንባታ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሚናን የተመለከተ የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዳሴ ግድብ ግንባታ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሚናን የተመለከተ የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው።

መድረኩ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና በታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ትብብር የተዘጋጀ ነው።

የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሙሳ አደም መድረኩ የፖለቲካ ልዩነቶቻችን እንዳሉ ሆነው በሀገራዊ ጉዳይ ላይ አንድ ላይ እንደምንቆም የምናሳይበት ነው ብለዋል።

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል።

በግድቡ ግንባታ ላይ ፓርቲዎቹ ሊኖራቸው የሚችለውን ሁለንተናዊ ድጋፍና ተሳትፎ እንዲሁም ሁለንተናዊ ሚና እና ብሄራዊ ጥቅምን የተመለከቱ ጉዳዮች ተነስተው እየተመከረባቸው ነው።
የዲፕሎማሲው እና የድርድሩ የእስካሁን ሂደትና የግድቡ ግንባታ ያለበት ደረጃም በመዳሰስ ላይ ነው።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.