Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቡዳፔስት ላይ በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ትውልደ ኢትዮጵያዊት የሆነችው እና በአሁኑ ጊዜ ለሆላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሐሰን በሩጫ ወቅት መውደቋ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም አትሌት ለተሰንበት ግደይ አትሌቷ ውድድሯን ጨርሳ ስተገባ እንዴት እንደሆነች በመጠየቅና አይዞሽ በማለቷ መልካም ተግባር ስለፈጸምሽ የዓለም አትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ ነሽ ተብላለች፡፡

በዚህ ጊዜ በሰጠችው አስተያየትም ሲፋን ስትወድቅ በጣም አዝኜ ነበር ፤ ሰዎች ሲደሰቱ እደሰታለሁ ሰዎች ሲያዝኑም አዝናለሁ ብላለች፡፡

በተሰጣት ሽልማትም የተሰማትን ደስታ ገልጻለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.