Fana: At a Speed of Life!

ከአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከተዋቀረ ጀምሮ በርካታ ሀገራዊ እና ከተማዊ ጉዳዮች ማለትም ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

ከፓርቲዎችና ከከተማ ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እየፈታ መሆኑ ይታወቃል። የምክር ቤቱ አባል የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማንኛውም ቡድንም ሆነ ግለሰብ ለሚመለከተው ለመንግሥት አካል አሳውቆ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሕገ መንግስታዊ መብት መሆኑን እንረዳለን።

የሚመለከተው የመንግሥት አካል ይህን ሕገ መንግስታዊ መብት ዜጎች ለመጠቀም ሕጋዊውን መንገድ ተከትለው በሚጠይቁበት ወቅት ሁሉ ተቀብሎ የማስተናገድ ሕገ መንግስታዊ ኃላፊነት እንዳለበት ለማስገንዘብ እንወዳለን።

በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች በሕገ መንግስቱ የተቀመጡ መብቶቻቸውን በተለይም የአደባባይ ሰልፎችን ለመጠቀም በሚያስቡበት ወቅት ሁሉ ሀገራዊ እና ከተማዊ የፀጥታ ሁኔታውን በመገምገም የሚደረጉ ሰልፎች ከፀጥታ አንፃር ሊያመጡ የሚችሉትን ጉዳቶች የመመዘን እና ሊያስከትል የሚችለውን ውጤት የመተንበይ ብሎም ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት የመስራት ኃላፊነት እንዳለባቸው መረዳት ይኖርባቸዋል ብለን እናምናለን።

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባደረገው ውይይት የሚከተሉትን ጥሪዎች ያቀርባል:-

(1). ሀገራችን እና ከተማችን ያለችበትን ሁኔታ ያላገናዘበ በሌሎች ለሁከት እና ለብጥብጥ መነሻ የሚሆን ሰልፍ መጠራቱ አናምንም። በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥያቄዎችን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ በማምጣት የሀሳብ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት ይቻላል። በመሆኑም የተጠራው ሰልፍ አግባብነት የሌለው እና ወቅቱን ያልጠበቀ መሆኑን ምክር ቤቱ ያምናል።
(2). የከተማችን ነዋሪዎች በተጠራው ሰልፍ ላይ የጋራ ምክር ቤቱ ተሳታፊ አለመሆኑን እና ወቅቱን ያልጠበቀ ጥሪ እንዲሁም ማሕበረሰብን ለእንግልት እና ለተጨማሪ ጫና የሚዳርግ ነው ብሎ ምክር ቤቱ ይረዳል።
(3). የመንግስት የፀጥታ አካላትም ሆኑ የከተማ መስተዳድሩ ፀጥታን ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ በከተማዋ ላይ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ሕግ ለማስከበር ሲባል ተጠርጥረው የተያዙ ዜጎች በሕግ አሰራር መሠረት ጉዳያቸው ተጣርቶ ትክክለኛ ውሳኔ እንዲያገኙ እንጠይቃለን።
4. የከተማችን ነዋሪዎች የራሱን እና የአካባቢውን ሰላም ከፀጥታ አካላት ጋረ በመሆን እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

ህዳር 29/2016 ዓ.ም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.